Tender Detail

Tender Details

  • Company በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት
  • Address አማራ፣ኢትዮጲያ, Phone: ----------
  • Website
  • Deadline15 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-12-15 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት ስር ለሚገኘው ግዳን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሪክእቃዎችን በሎት ድምር ህጋዊና ብታት ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት ስር ለሚገኘው ግዳን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሪክእቃዎችን በሎት ድምር ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡-

1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እታ ዘርፍ ላይ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የማንኛውም የግዥ መጠን ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡ ከብር 20 ሺህ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት 15% ግማሹን /50%/ እና ከተከፋይ ሂሳብ ላይ 3 % ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ይቆረጣል፡፡

2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ዓይነት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዘመን የምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት በደሴ ከተማ በአስተዳደርና ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 16 እና ዘመን አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ለአንድ የጨረታ ሰነድ በብር 200.00 መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበትቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አልቆ በ15ኛው ቀን ማግስት በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት/ደሴ ከተማ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፣ ተጫራቾች በአለቱ ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ያልተገኘ ተጫራችም በጨረታ ሂደቱ ተገዥ ይሆናል፡፡

4. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደሩበትን የእቃ ዓይነት ስፔስፊኬሽን አይቶ በትከክል ዋጋ በመሙላት የሚጫረቱበትን ዋጋ በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸነ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ደሴ ከተማ በሚገኘው በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት ግዥ አፈሰር ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ከማሸጊያው ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ማንኛውም ተጫራቶች ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2%/ሁለት ፐርሰንት) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /cpo/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

7. አሸናፊው ሲታወቅ ላሸነፈው እቃ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /በCPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በማስያዝ ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ እና የቴስት ማሰሪያ ወጭን ጨምሮ ተጫራቹ ችሎ የእቃውን ጥራት በአማካሪ በማረጋገጥ እና ቴስት ለሚያስፈልጋቸው ግብአቶች ቴስት በማሰራት ማለፉ በአማካሪ በማረጋገጥ ያሸነፈውን እታ ፕሮጀክቶቹ በሚገኙበት መጋዘን ድረስ ገቢ ማድረግ ግዴታ ነው፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ማቅረብ እንዳለበት ተገንዝቦ ዋጋ መሙላትና መወዳደር ያለበት ሆኖ የሚሞላው የ 1 ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በሚሸጠው ጨረታ ሰነድ ዋጋ መሙያ ፎርም መሰረት ቫትን ያካተተ መሆን ሲገባው በስከርቢቶ ቫት ይጨመርበት ተበሎ ከተጻፈ ተጫራቹ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።

9. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር በጥንቃቄ ይሞላ፡፡ በአጋጣሚ ስርዝ ድልዝ ከተፈጠረም ፓራፍ ይደረግ። ተጫራቶች እኩል ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ ነኛ ብዛት ላሸነፈው ቅድሚያ ይሰጣል እንደዚያም ሆኖ እኩል ከሆኑ በእለቱ በተገኙት ተጫራቾች ፊት በእጣ ይለያል። ተጫራች ካልተገኘም እጣው በኮሚቴው ይጣላል።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ሆኖ ተጫራቹ በዚህ ምከንያት ለሚያወጣው ወጪ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስ.ቁ 033124973/03331009 ወይም 011265652 አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ይጠይቁ፡፡

አድራሻ ደሴ ካራ ጉቱ ግብርና ፊትለፊት ከሚገኘው ምስ/አማ/ማስ/ጽ/ቤት፣ ኤ.አ ለገሀር አመልድ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ዘመን ኢእ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት

Save Tender