በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ለ2018 የበጀት ዓመት ለሚያስተምራቸው ተማሪዎች ለምግብ እገልግሎት የሚውል አቅርቦት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Kombolcha College of Agriculture (ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ለ2018 የበጀት ዓመት ለሚያስተምራቸው ተማሪዎች ለምግብ እገልግሎት የሚውል አቅርቦት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ለተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ማለትም - ሎት1 የተለያዩ አትክልቶች (ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ቃሪያ፣ የወጥ ድንች፣ ጥቅል ጎመን እና ካሮት ) ሎት2 የባልትና ውጤቶችን (አተር ክክ፣ ምስር ክክ፣ ምጥን ሽሮ ፣ በቂ ቅመም ያለው የተዘጋጀ በርበሬ እና የተፈጨ ጎመን ዘር)፣ ሎት3 ዳቦ፣ ሎት4 ሸቀጣሸቀጥ (ቲማቲም ድልህ /ሳልሳ/ 850 ግራም፣ 1ኛ ደረጃ ሩዝ፣ ፖስታ ባለ 500 ግራም፣ የምግብ ጨው፣ ማርማላታ፣ ሻይ ቅጠል ባለ100 ግራም) ሎት5 የተፈጨ የበሬ ስጋ፣ ሎት6 ሰርገኛ ጤፍ ወዝ ያለው 1ኛ ደረጃ የሆነ ሎት7 ለምግብ አገልግሎት የሚውል ዕንቁላል፣ ሎት8 ስኳርና ዘይት፣ በሎት 9 ተፈልጦ የተዘጋጀ ለማገዶ እንጨት የሚውል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ከላይ ከሎት 1 እስከ ሎት 9 የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለማቅረብ አግባብ የሆነና በየዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ በደንብ በሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር በተናጥል A4 ወረቀት በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፀውንና በየዘርፉ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 10 መግዛት ይቻላል።
- ከአንድ ዘርፍ በላይ ለምትሳተፉ ተጫራቾች ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደተጫራቹ ምርጫ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የጠቅላላ ዋጋ ግምት 1% ቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 1/4/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 12 ዘወትር በሥራ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ በታሸገ ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል በማለት የድርጅታቸውን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታውም በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0335510186 /0335514206 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ (ወሎ)
