የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌከትሮኒከስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የግልፅ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌከትሮኒከስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች 23/03/2018 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች :-
1. በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
2. ለሐራጅ ጨረታው 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ(C.P. O) ማቅረብ የሚችል፤
3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤
4. በሐራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ ራሱ ያቀርባል፤
5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ዕቃ ከፍያውን በዐ5 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤
7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
8. በጨረታው ያላሸነፈ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
9. አሳማኝ የሆነ ምከንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
10.ማንኛውም ተጫራች ዕቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
11.ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
12.ተጫራች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከ23/03/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው ከ25/03/2018 ዓ.ም 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
13.የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው 25/03/2018 ከጠዋቱ 4፡15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤
NB፦ አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት ) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
