Tender Detail

Tender Details

  • Company የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-1873
  • Website
  • Deadline10 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየሰጡትን ዋጋ 1/0ኛውን
  • opening date2025-12-10 00:00:00
  • Categories Vehicle

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዛቸውን ተሸከርካሪዎች ለመሸጥ ይፈልጋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዛቸውን ተሸከርካሪዎች ለመሸጥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁ.05/2018 የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋይ የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ሕጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው በታክስ አከፋፈል አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ከጀነሲስ ፋርማስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ 2 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. በግልጽ ጨረታው የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ በግልጽ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትርበሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት - 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ከቴሌ ከፍ ብሎ ቅ/ጽ/ቤቱ አዲስ ባስገነባው ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይኖርብዎታል፡፡
  3. ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/0ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ስም (Ministry of Revenue በAdama Branch Office) በባንክ አሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡

 

ተ.ቁ

የመ/ቤቱ ስም

ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት

የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ

የተለያየ ሞዴል ያላቸው 2 ተሽከርካሪዎች

ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት

ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

 

  1. የጨረታ መክፈቻ ቦታ:- በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ከቴሌ ከፍ ብሎ ባስገነባው አዲሱ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳዳር ቢሮ ቁጥር 403 ሲሆን ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  2. የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
  3. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፈሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  4. የተሸከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀናት ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡
  6. ከላይ በተ.ቁ 9 በተገለጸው ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  7. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልጽ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 022-211-1873/ 022-211-1728 እና 022-211-0762 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender