Tender Detail

Tender Details

  • Deadline04 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security5%
  • opening date2025-12-04 00:00:00
  • Categories Vehicle

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የግልፅ ጨረታ ቁጥር 02/2018

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

በግልፅ ጨረታ ቁጥር 02/2018 በ25/03/2018 ዓ.ም ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረበውን ተሽከርካሪዎችን ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች -

  1. ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ዲጅታል /ብሔራዊ መታወቂያ ያለው
  2. ለጨረታ የቀረበው ተሽከርካሪ ሲሆን የሚገኘው ድሬዳዋ ሙዲአነኖ ግቢ በሚገኘው ተሸከርካሪ መጋዘን ውስጥ ነው።
  3. የተሽከረካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የሆነ ሰው በጨረታ መሳተፍ አይችልም፡፡
  4. በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰእት ከማክሰኞ 16/03/2018 ጀምሮ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 12 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰእት እስከ 6 ሰዓት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት እና ሪሲት በመውሰድ ተሸከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል።
  5. ተሽከርካሪውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  6. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድሬዳዋ ሙዲአነኖ የሚገኘው ግቢ ውስጥ ነው።
  7. ተጫራቾች ለተሽከርካሪው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት።
  8. ተጫራቾቾ ተሸከርካሪውን ለመግዛት ለጨረታው ዋስትና ማስከበረያ 5% በንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምረክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ የሞሉትን የጨረታ ሰነድ እና ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 3:45 ድረስ በድሬዳዋ ሙድእነኖ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  10. ጨረታው ከጠዋቱ 3:50 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ሙድእነኖ ጉምሩከ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ሳጥኑ ይከፈታል።
  11. በጨረታው እሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቶች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  12. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሸከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል።
  13. ከላይ በተራ ቁጥር 12 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሽከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበረያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
  14. የጉምሩክ ኮሚሽን ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915460970 (0912885746) መደወል ይቻላል።

 

የኢትዮጰያ ጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender