በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፈያ ዲቪዥን የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ የተሽከርካሪ የተበላሹ እቃዎች የማሽን ሾፕ ሥራ አገልግሎት ማከነወን የሚችሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለአንድ አመታት ውል በማሰር ማሰራት ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AAWSA/WSIDD/GOV/NCB/NCS002/2018
በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፈያ ዲቪዥን የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ የተሽከርካሪ የተበላሹ እቃዎች የማሽን ሾፕ ሥራ አገልግሎት ማከነወን የሚችሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለአንድ አመታት ውል በማሰር ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አገልግሎት አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ልደታ በሚገኘው የሕዝብ መናፈሻ ጎን የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ በሚገኘው የዲቪዥኑ ቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድርስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት መወዳደሪያ ፖስታው ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ የጨረታ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ60 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል። ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሠነድ ጋር በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ውል በተፈረመ በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ይኖርበታል።
- የተጫራቾች የመወዳደሪያ ሠነድ ለ60 /ስልሣ/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት። ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
- የጨረታ ሠነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
- ጨረታው ታኅሳስ 14/2018 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ በ8፡30 5ኛ ፎቅ ዲቪዥኑ ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳዳሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም።
- እያንዳንዱ ተጫራች ዲቪዥኑ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት መሰረት ግልጽ በሆነ መልኩ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል። የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት። ይህንን ያልገለፀ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
- ዲቪዥኑ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን የአገልግሎቶች ግዥ በ20% የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዲቪዥኑ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ-08 ፣ የቦታው ልዩ ስም፡- ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ
ስልክ ቁጥር:- +251 11 5579512/9036 (1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል)
በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን
