Tender Detail

Tender Details


የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግሥታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ እያስገነባቸው ላሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል ለደ/ማርቆስ እና ለደ/ብርሃን ጠ/ሆስፒታል የትራንስፎርመር አቅርቦትና ገጠማ፤ ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አቅርቦት፣ ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውል የፈርኒቸር እቃዎች አቅርቦት፣ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

Menkorer Construction Enterprize (የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)


 

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግሥታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ እያስገነባቸው ላሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል ለደ/ማርቆስ እና ለደ/ብርሃን ጠ/ሆስፒታል የትራንስፎርመር አቅርቦትና ገጠማ፤ ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አቅርቦት፣ ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውል የፈርኒቸር እቃዎች አቅርቦት፣ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

  • ምድብ 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አቅርቦት
  • ምድብ 2 የፈርኒቸር እቃዎች አቅርቦት
  • ምድብ 3 ለደ/ማርቆስ እና ለደ/ብርሃን ሆስፒታል የትራንስፎርመር አቅርቦትና ገጠማ

በዚህም መሰረት፡-

    1. ተጫራቾች የምትጫረተበትን ሰነድ ያንዱን ዋጋ በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር13 ማስገባት አለባችሁ።
    2. ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ሰዓት ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻው በበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመክፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
    3. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር የዘመኑን ግብር የገበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
    4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደ/ማርቆስ ከተማ ከሚገኘው መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 እና አዲስ አበባ 4 ኪሎ አልማ ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ብር 200 ሁለት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤ ሆኖም የጨረታ ፖስታ ገቢ የሚሆነው ደ/ማርቆስ ከተማ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ነው።
    5. በየምድቡ የሚወዳደሩ ተጫራቶች ፋይናንሻል፣ ኦሪጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
    6. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ የጠ/ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
    7. አሸናፊው ድርጅት በምድብ 3 የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ የመድን ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
    8. አሸናፊ ድርጅት በምድብ 1 እና 2 ላይ ያሸነፋቸውን እቃዎች የተዘረዘሩትን በራሱ ትራንስፖርት በድርጅቱ ዋና ቢሮ በማቅረብ ማስረከብ አለበት፡፡
    9. አሸናፊው ድርጅት ምድብ 1 ላይ ያሉትን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በተያያዘው ስፔስፊኬሽን ወይም ዝርዝር መሰረት ማቅረብ አለበት፡፡
    10. አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው እቃዎች እና የሚሠራው ሥራ በባለሙያ ተረጋግጦ ማለፍ አለበት።
    11. አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል፡፡
    12. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
    13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0920514407 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት

 

Save Tender