Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 011-157-58-43
  • Website
  • Deadline08 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening date2025-12-08 00:00:00
  • Categories Cloth And Shoes , System Supply And Installation

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ደንብ ልብስ & SUPPLY AND INSTAL-LATION ID card Printer for Resident ID Card Production Turnkey basis ልዩ ልዩ እቃዎች መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ


ግልፅ ጨረታ 4/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ደንብ ልብስ & SUPPLY AND INSTAL-LATION ID card Printer for Resident ID Card Production Turnkey basis ልዩ ልዩ እቃዎች መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ለዕቃ አቅራቢነት የሰጠውን ምዝገባ የምስከር ወረቀትና የተጨማሪ አሰት ታክስ (VAT) ተጠቃሚ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 15/308 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በጥሬ ገንዘብ በመከፈል የጨረታ ሰነድ በመ/ቤታችን ከፍያና ሂሳብ ዳሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር

ሎት:1 2,000.00/ሁለት ሺህ ብር ብቻ/

ሎት 2 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ/

ሎት3-10.000.00/አስር ሺ ህ ብር ብቻ/በቀረበው ዝርዝር መሰረት በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው:

4. የጨረታውን ሰነዶች ዋጋ የሰጠበትን ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም መስሪያ ቤታችን በሚያዘጋጀው የቴክኒክ ፍላጎት መግለጫ መሰረት አንድ አሪጅናልና አንድ ኮፒ በማዘጋጀት በድምሩ በአራት ፖስታ ለየብቻ ታሽጐ ባዘጋጀነው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡

5. ጨረታው 23/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት በመ/ቤቱ ሚኒ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙነት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ወይም ስፔስፊኬሽን የተጠየቀበት ማቅረብ አለበት፡፡ ለማቅረብ አስቸጋሪ የሆኑትን ዕቃዎች በአካል ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡

7. በጨረታው አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ መ/ቤቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡

8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቶች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

10. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ ስልሳ የሥራ ቀናት ነው፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሀጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. ፋይናሻል ዋጋ መሙላት የሚቻለዉ ተቋሙ ባዘጋጀዉ ሰነድ ብቻ ነዉ፡፡

13. ተጫራቶች በሚወዳደሩበት የእቃ አይነት ለአንድ እታ አንድ ሳምፐል ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡በአንድ እቃ ሁለት አይነት ሳምፐል ያቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋሉ፡፡

ማሳሰቢያ፣

 

የሚገዛው ዕቃ ዝርዝር ከዚህ የጨረታ ሠነድ ጋር የተያያዘ ስለሆነ በተዘጋጀው የዕቃ ዝርዝር መሰረት በእያንዳንዱ ተራ ቁጥርየምታቀርቡበትን የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ እንዲገለጽ እና ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ፍላሽ ይዘው በመምጣት በሶፍት ኮፒ እንዲወስዱ እናሳስባለን፡፡

አድራሻችን፡ አዲሱ ገበያ ሸገር መናፈሻ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው::

ስልክ ቁጥር፡- 011-157-58-43

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ

Save Tender