የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ ለባህር ዳር ዙሪያ ክላስተር ፕሮጀክቶች፣ ለደብረ ታቦር ጥገና ጽ/ቤት እና ለክላስተር ፐሮጀክቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈለጋል፡፡
Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
የማሽነሪ አና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
ድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ ለባህር ዳር ዙሪያ ክላስተር ፕሮጀክቶች፣ ለደብረ ታቦር ጥገና ጽ/ቤት እና ለክላስተር ፐሮጀክቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈለጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳሩ ተጋብዘዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚቀርቡት ተሸከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተዉ መቅረብ አለባቸው።
- የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለሰርቪስ መኪና በቀን፡ ገልባጭ መኪና በሰዓት፡ ለውሃ ቦቱ በሰዓት ለገልባጭ መኪና በሜ.ኩብ እና ሎቤድ በኪ.ሜትር ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮንስትራሽን ኤጀንሲው ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኮፒውን ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ/ ብር ብቻ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ስም በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል ገቢ በማድረግ የባንከ ዲፖዚት ስሊፕ ኮፒውን በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 29/03/2018 ዓ.ም ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ አፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 29 /03/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንስትራክሽን ኤጄንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ አፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በ29/03/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ባለው ቦታ ላይከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 058-222-11-00 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-320-55-55 ወደም 058-222-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ድረ ገጽ www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
