Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ቦረና ጉጂ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-3350901
  • Websitehttps://www.oromiaforest.et/
  • Deadline05 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-12-05 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን ከዚህ በታች በጥቅል ስም የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግል አሮጌ ብረታ ብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን ከዚህ በታች በጥቅል ስም የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግል አሮጌ ብረታ ብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች

1.     ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.     በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

3.     የተጨማሪ እሴት ታክስ / ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ ቁጥር የተሰጣቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ 2% በተመሰከረለት ቼክ ወይም CPO /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ ተከታታይ የስራ ቀናት በቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡

5.     የጨረታው ሳጥን በ 11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡

6.     ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ሞዴል ወይም አይነት በጨረታው ሰነድ ላይ በግልጽ መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት የሁሉንም ናሙና ይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7.     ማንኛውም ተጫራች ለመንግስት ግዢ ያልታገደ መሆን አለበት፡፡

8.     በተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ያሳግዳል፡፡

9.     ጨረታው በሚከፈትበት ሰአት ከላይ የተጠቀሱትን አስፈላጊ መረጃዎች አሟልተው ባልተገኙ ተወዳዳሪዎች ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ፡፡

10. አሸናፊው ያሸነፈዉን እቃ በራሱ ወጪ አጓጉዞ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 046-3350901 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender