በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ የጽህፈት መሣሪያ፣ የጀነሬተር መለዋወጫ፣ ደንብ ልብስ እና የኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም የሶላር እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ የጽህፈት መሣሪያ፣ የጀነሬተር መለዋወጫ፣ ደንብ ልብስ እና የኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም የሶላር እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች አንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የማችል፣
- ለጨረታ ማስከበረያ ሲፒኦ /CPO / 10,000/ አስር ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነድ ጋር የሚያቀርብ ሆኖ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሊመጡ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እና የተጫራቹን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ መያዙን አይዘንጉ፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ዶክመንት ኦርጅናል እና ኮፒ በማያያዝ በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት ግዥ ፋ/ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ውስጥ በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ ይዘው በመገኘት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀለት ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚዘጋው በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡ አሸናፊው እቃውን የሚያስረክብበት ቦታ በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- ጨረታናው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቦታ በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት ሆኖ የድርጅቱ ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በዕለቱ ባይገኙ የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ 0473310669 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት
