በደቡብ ኢት/ያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ ለማስጠገንና የደን ዘር ዓይነቶችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢት/ያ ክልል መንግስት ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢት/ያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ ለማስጠገንና የደን ዘር ዓይነቶችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 9 የተለያዩ መኪናዎችና ማሽኖች ጥገና፣ ሎት 15 የሞተር ሳይክል ጥገና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ፣ ሎት 16. የደን ዘር ዓይነቶችና የአቮካዶ ምርት ሰጪ ግንድ፣ ሎት 17 የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉት፡-
- በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ ሥራዎች አገልግሎቶች ከአሰሪው እካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ።
- የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) ብር በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ። ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡ : 16ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለሎት ዘጠኝ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ ለሎት አስራ አምስት 10,000 (አስር ሺህ ብር)፣ ለሎት አስራ ስድስት 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ለሎት አስራ ሰባት 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ርክብከብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሆናል።
- የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0461800863 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ
