የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የተለያየ ዓይነት አገልግሎት የማይሰጡ መኪኖች እና ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የተለያየ ዓይነት አገልግሎት የማይሰጡ መኪኖች እና ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ።
- ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻ በክልሉ በሚገኙ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ እና ዱራሜ ከተሞች ሲሆን ዝርዝር አድራሻ መረጃቸው በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልጸዋል።
- በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 /አስራ ስድስት/ ቀናት ለእጩ ተወዳዳሪዎች ከፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል።
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ/ ብር በመክፈል ከቢሮው መንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከንብረት ዋጋ ጥናትና ማስወገድ ዳይሬከቶሬት ክፍል በመንግስት የስራ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
- ንብረቶቹን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ በቆሙበት ቦታ ተገኝቶ ማየት ይቻላል።
- ተጫራቾች መጨረቻ ሰነዳቸውን ኦርጂናልና ኮፒ ዶክመንቶችን በመለየት በጥንቃቄ ለየብቻ በኤንቨሎፕ /ፖስታ በማሸግ እስከ 16ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራች በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ በመቅረቱ የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚገዙት ንብረት ዓይነት ጠቅላላ የመግዣ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ስም አዘጋጅተው ከመወዳደሪያ ኦርጂናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊው እንደታወቀ ለተሸናፊው ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ተመላሽ ይደረግለታል።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
- ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0913735367/0910928986 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት /ሆሳዕና
