በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ምክር ቤት ጽ/ቤት ለም/ቤት አዳራሽ የሚሆን ሞንታርቦ ከነ ሚክሰር ከአቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ምክር ቤት ጽ/ቤት ለም/ቤት አዳራሽ የሚሆን ሞንታርቦ ከነ ሚክሰር ከአቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- በዘርፋ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
- የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች እና ክሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀረበ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ አለባቸው። በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፈደል የተገለጸው ይወሰዳል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200) በመክፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 /አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ (1) ኦርጂናል እና ሁለት (2) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ (1) ኦርጅናል እና ሁለት (2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅርብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል። ያለበለዚያ ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች በእያንዳዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው ቀን ከሰዓቱ 9፡00 ሰአት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
ደ/ወርቅ ስልክ:- 0966886973/0910997747/0929241731 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ። ጽ/ቤቱ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
