የሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ.ም የባጀት ዓመት አዲስ ለተቋቋመው ካምፓስ ለተማረዎቸ ምግብ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሸገር ኢንስቲትዩት ቴክኖሎጂ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ሸ/ኢ/ቴ /01/2018/1
የሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ.ም የባጀት ዓመት አዲስ ለተቋቋመው ካምፓስ ለተማረዎቸ ምግብ የሚውል
- ሀ. ለምግብ የሚውል የተለያዩ ጥሬ ሰብሎች
- ለ. የተለያዩ አትክልቶች እና ፍራፍሬዎች
- ሐ. የተለያዩ ጣፋጮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ወይንም አቅራቢዎች እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- የታደሰ እና በግዥው ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው።
- በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ህጋዊ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና የከፈሉበትን ማስረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተመዘገቡ እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት በስራ ሠዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) ኮዬ ፈጬ ካደባባይ ወደ ክ/ከተማ ገባ ብሎ የምጎኝ የኢንስቲትዩት ካምፓስ በሚገኘው የግዥ እና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒክ እና ፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦሪጂናሉን እና ኮፐውን በተለያዩ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው፡፡
- ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀን በአየር ላይ ውሎ በአስራ ስድስተኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ6፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8:00 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ አስራ ስድስተኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በተወዳደሩበት ዘርፍ ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ቼክ (CPO) ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖረባቸዋል፡፡
- የሚያቀርቡት ሠነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ ግዥ ቡድን መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ኢንስቲትዩቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ኮዬ ፋጬ አደባባይ ወደ ክ/ከተማ ገባ ብሎ የምገኝ ካምፓስ
የሸገር ኢንስቲትዩት ቴክኖሎጂ
