የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀከት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU/PPM/Dis/01/2018(NCB)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀከት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ፡-
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኃላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንከ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.ኤ.አ. ፕሮ ክት ፖርትፖልዮ ማኔጅመንት ወይም EU-PPM ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለቸው፡፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EU/PPM⁄ Dis/01/2018 NCB የሚል ምልክት በማድረግ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ነው በመቅረብ በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከ7፡00 እስከ 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎች በሚገኙበት ዕቃ ግምጃ ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል፣
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ይመልከቱ።
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 127 5503 መደወል ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀከት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
