Tender Detail

Tender Details

  • Company Ministry of Revenues (የገቢዎች ሚኒስቴር)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-617-84-90
  • Websitehttp://WWW.MOR.Gov.et
  • Deadline03 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityየሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን
  • opening date2025-12-03 00:00:00
  • Categories Vehicle

የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ከሶላር ዩስክ ሶሉሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፤ ከአፍራ አስመጪና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከጋንፋር ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከሎኒ አግሮ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፤ ከዲኤስኬ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፤ ከጄቢ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ከአቶ ተከኤ ዘርአይ የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ministry of Revenues (የገቢዎች ሚኒስቴር)


 

በታክስ ዕዳ የያዛቸውን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ልዩ ሞዴል

ያላቸው ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ-03/2018

የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ከሶላር ዩስክ ሶሉሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፤ ከአፍራ አስመጪና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከጋንፋር ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከሎኒ አግሮ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፤ ከዲኤስኬ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፤ ከጄቢ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ከአቶ ተከኤ ዘርአይ የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

1. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ(ፓስፖርት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ህንፃ "ለ" 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬከቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ “ሀ” 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከታከስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል፡፡

3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Mirstry of Revenue) በባንከ አሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡

ተ.ቁ

   የመ/ቤቱ ስም

ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት

የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ገቢዎች ሚኒስቴር

የተለያዩ የቢሮ መልገያ ዕቃዎች፣የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች፤ በሶላር የሚሠሩ ቴሌቪዥኖች፣ ሶላር ቦርዶች ፣ሶላር ፍሪጅ እና የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች

ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት

ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ ዚያኑ ቀን 4፡00 ሰአት ይከፈታል፡፡

5. የጨረታ መከፈቻ ቦታ- መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች /ህጋፍ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል ።

 

6. የግልፅ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታ መከፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡

7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋርእንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃው አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስሙ-ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች ሻጭን አይመለከትም፡፡

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፋበትን ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል=

10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾ የግልፅ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

11. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበፍ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-617-84-90 ኮድ (2044) (2045) (2046) የውስጥ መስመር (EXT 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MOR.Gov.et መመልከት ይቻላል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር

Save Tender