በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ/ም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ፡- 1 መድኃኒቶች እና ሬጀንቶች 2. የደንብ ልብሶች 3. የጽዳት እቃዎች 4. የተለያዩ የጽሕፈት እቃዎች 5. የሠራተኛ ካፌ አገልግሎት /የምግብ እና መጠጥ አቅርቦት/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በቂርቆስ ክፍስ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የቂርቆስ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ/ም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ፡-
1 መድኃኒቶች እና ሬጀንቶች 2. የደንብ ልብሶች 3. የጽዳት እቃዎች 4. የተለያዩ የጽሕፈት እቃዎች 5. የሠራተኛ ካፌ አገልግሎት /የምግብ እና መጠጥ አቅርቦት/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችል ማንኛውም ሕጋዊ የንግድ ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ቅጥር ጊቢ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር301 በሥራ ሰዓት በመቅረብ እና የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብርብቻ) በመከፈል እና የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በመውሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ጨረታው በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
የጨረታው መስፈርቶች:-
1. በግብር ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ መያዣ የሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) በጤና ጣቢያው ስም በተዘጋጀ ሲፒአ (CPO) ኮፒው ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት አስፈላጊውን የትብብር ደብዳቤ ለመወዳደርየሚከፈተው ፖስታ ማለትም በኮፒው ውስጥ በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
5. አሸናፊው የንግድ ድርጅት የጠቅላላ ዋጋውን 10% በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅበታል።
6. ኦርጅናል ፖስታ በጨረታ መወዳደሪያ ወቅት አይከፈትም።
7. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ድረ-ገጽ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዝርዝር ጤና ጣቢያው ባቀረበው የዋጋ ሰንጠረዥ ላይ በመሙላት እና እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋጋውን እና ኮፒውን በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።በተጨማሪም ቴክኒካል ሰነድ ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ በድጋሚ በአንድ ፖስታ መታሸግ አለበት።
9. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሁሉም ተጫራቾች ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋርማቅረብ አለባቸው።
10.ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።
11. ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችለው ከንግድ ፈቃድ ጋር ተያያዥነት ባላቸው አቅርቦቶች/አገልግሎቶች ላይ ብቻ ነው።
ማሳሰቢያ- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የሚቀርቡት ዋጋዎች ተጨማሪ እሴት ታክስን/ተርን ኦቨር ታክስን ያካተቱ መሆን አለባቸው፡፡
አድራሻ:- ከሜከሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ከገነት ሆቴል ወደ ሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚያስገባው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0115536456/0115156192 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ
