የኢትዮዽያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮዽያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ጋቢናዎቹን ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒከ ማዕከል በመገኘት ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት (ETHIOPIAN INSURANCE CORPORAION) ስም ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። የማስያዣ ዋጋው የጨረታ መነሻውን 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የጋቢና የማስያዣ ዋጋ ብር 1000 ነው።
ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታከስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው በማዕከሉ ግቢ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴከኒክ ማዕከል ይከፈታል። በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን፣ ለአሸናፊዎች ግን ሂሣቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የገዙትን ዋጋ አጠናቀው በıo ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ።
የጨረታው አሸናፊ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ከከፈለ በኋላ ንብረቱን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላነሳ ከከፍያው ላይ የቅጣት ተቀንሶ ቀሪ ሂሳብ ካለው ተመላሽ ይደረግለታል። ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ጋቢና በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011439-25-89 እና 011439-25-45 መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮዽያ መድን ድርጅት
