በኢትዮጵያ ኤሌከትሪከ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ከዚህ በታች የተገለጹትን አገልግሎት የማይሰጡ ቁርጥራጭ የአልሙኒየም ሽቦዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢኤአ-ባሪ/ግብጨ/009/2018
በኢትዮጵያ ኤሌከትሪከ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ከዚህ በታች የተገለጹትን አገልግሎት የማይሰጡ ቁርጥራጭ የአልሙኒየም ሽቦዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሕር ዳር በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌከትሪክአገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ዋና መ/ቤት ቀበሌ 05 ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት ወይም ድብ አንበሳ ሆቴል ጎን በሚገኘው ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር408 በመምጣት ለአንዱ ሎት ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በድጋፍ ደብዳቤ የሚመጡ ተጫራቾችን አናስተናግድም።
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡
5. ጨረታው ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰፕላይ ቼይን፣ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 408 ይከፈታል።
6. ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልከ ቁጥር 058-320-6999/6775 መደወል ይችላሉ፡፡
7. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባሕር ዳር ሪጅን
