Tender Detail

Tender Details

  • Company AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
  • Address ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4403766
  • Website
  • Deadline27 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security5%
  • opening date2025-11-27 00:00:00
  • Categories Machinery

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው የኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ (ዱከም) የሚገኙ የሶስት የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ማሽነሪዎች ማለትም (used warping machine fused high temperature &high-pressure intelligent dye machine used knitting machine! Used electric steam boiler: Used industrial washing machine Used Centrifugal hydro-extractor: Used pneumatic Steaming Machines used printing & dyeing production line machine fused embossing machine እና ሌሎችም) እንዲሁም የዳይፐር ማምረቻ ፋብሪካ ማሽነሪ ማለትም (used Baby diaper production making line machine) በተጨማሪም የፋብሪካዎቹ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ የቀረቡ ማሽነሪዎችና የቢሮ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 24/2018

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው የኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ (ዱከም) የሚገኙ የሶስት የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ማሽነሪዎች ማለትም (used warping machine fused high temperature &high-pressure intelligent dye machine used knitting machine, Used electric steam boiler: Used industrial washing machine Used Centrifugal hydro-extractor: Used pneumatic Steaming Machines used printing & dyeing production line machine fused embossing machine እና ሌሎችም) እንዲሁም የዳይፐር ማምረቻ ፋብሪካ ማሽነሪ ማለትም (used Baby diaper production making line machine) በተጨማሪም የፋብሪካዎቹ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሐሙስ ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡ በመሆኑም፤

1. በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋርአያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡

3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሐሙስ ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትርበስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4. በዕቃ ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼh (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

 

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ኢ.አ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት

 

የእቃ ግልፅ

 

እስከ 17/03/2018

18/03/2018 3: 45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል፡፡

 

6. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡ ኢአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት (ናይል ኢንሹራንስ ህንጻ) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡

7. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን ዕቃ በራሳቸው ወጪ ከፋብሪካው የማንሳት፣ የመጫንና የማጓጓዝ ግዴታ ይኖርባቸዋል።

9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ዉስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

10. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩከ ፡- 011 - 470 - 85- 03 ማሳሰቢያ፡- ዕቃዎቹን ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን(ዱከም) በአካል በመሄድ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የጨረታ ሰነድ መሸጫ አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ከ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender