የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል ዓመታዊ የተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
Sidama National Regional State Road Development &Transport Bureau (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል ዓመታዊ የተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈርት መሠረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የአቅርቦት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ሆኖ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸዉ።
- የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5,000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) በC.P.O ወይም ህጋዊ ባንክ ጋራንቲ (Unconditional Bank Guarantee) ለ90 ቀን ፀንቶ የሚቆይ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ በሁለት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ላይ ብቻ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ በቴክኒካል ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ለ3 ወራት (90 ቀናት) ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) ከፍሎ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 104 በአካል ቀርበው መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች በመ/ቤቱ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ ብቻ የእጅ ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 0462121455/ 0462122050 ደውለው ይጠይቁ።
ሀዋሳ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ
