Tender Detail

Tender Details

  • Company አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን
  • Address ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113301519
  • Website
  • Deadline27 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security350,000 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺ ብር/
  • opening date2025-11-27 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን ለ2018/19 የምርት ዘመን የሚውል ዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ በጉራጌ ዞን ላሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለማሠራጨት ህጋዊ የሆኑ ሀገር ውስጥ ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን


 

የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አድገዩ/001/2018 ዓ.ም

 

አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን ለ2018/19 የምርት ዘመን የሚውል ዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ በጉራጌ ዞን ላሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለማሠራጨት ህጋዊ የሆኑ ሀገር ውስጥ ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች ማሟላት የሚችል በዘርፉ የተሰማራ ማንኛውም የሀገር ውስጥ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅት በጨረታው መሳተፍ የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው ማረጋገጫ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፍል የጨረታውን ሰነድ ከአድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዬን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዩኒዬኑ ፅ/ቤት ድረስ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰአት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 350,000 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺ ብር/ ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከዩኒየኑ ሂሳብ ክፍል የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8:00 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 8:30 በዩኒየኑ ጽ/ቤት ይከፈታል።
  5. ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱን ህጎች ማከበር የሚችል መሆን አለበት።
  6. ዩኒየኑ በትራንስፖርት ጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. ተጫራች ድርጅት ከዚህ በፊት በአድማስ ኃላ/የተ/የገ/ኅ/ስራ ዩኒየን የወጡ ጨረታዎችን ካሸነፈ በኋላ ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ መሆን አለበት፡፡
  8. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር፡- 0113301519/0936780943/091277538 1 በመጠቀም ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  9. አደራሻ፡- ጉራጌ ዞን ወልቂጤ፤

 

አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን

 

Save Tender