Tender Detail

Tender Details

  • Company በሸገር ከተማ አስተዳደር የገፈርሳ ጉጂ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ገፈርሳ ጉጂ በሸገር ከተማ አስተዳደር ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 49 53 95 45
  • Website
  • Deadline01 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price600.00
  • Bid Security300,000.00
  • opening date2025-12-01 00:00:00
  • Categories Construction Machinery , Vehicle

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚወሉ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች ፤ ደብል ጋቢና ፒካፕ መኪና ተሸከሪካዎች የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገፈርሳ ጉጂ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2018

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚወሉ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች ፤ ደብል ጋቢና ፒካፕ መኪና ተሸከሪካዎች የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ዝርዝር ሁኔታዎች

የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከገፈርሳ ጉጄ ከ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ ቤት የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በሲንቄ ባንክ በተከፈተው ሒሳብ ቁጥር1065173571213 7ቢ በማድረግ ዲፖሲት ሲሊፑን/ deposit slip/ ገፈርሳ ጉጄ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ ቤት ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን ገፈርሳ ጉጄ ከ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር አወጋገድ እና ጠቅላላ አገልግሎት ሂደት ከፍል ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የተጫራቾች ገዲታዎች

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣ እንዲሁም በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተመሰከረ CPO (ሲፒአ) ብቻ 300,000 ብር ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

5. ለማሽነሪ ኪራይ ላይ የሚሳተፍ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ነዳጅን፤ ቅባት፤ ጥገናውን እና ሌሎች ተዛማጅ ወጪዎችን በተጫራቹ ድርጅት (አከራይ) የሚሸፈን ይሆናል።

6. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ማሽነሪዎችን በራሳችሁ ወጪ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ/ሥራ የሚሠራበት ቦታ/ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ጨረታውን ላይ የሚያቀርቡት ማሽነሪ ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ወይም ህጋዊ የኪራይ ውል አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል።

8. አሸናፊ የሆኑ ተጫራች ውል ሲፈርሙ ማስከበሪያ (ዋስትና 10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

 

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በአርጅናል እና በኮፒ በመለየት በታሸገ ፓስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የስራ ቀን እስከ 15ኛው የመንግስት ሥራ ሰዓት በገፈርሳ ጉጄ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር አወጋገድ እና ጠቅላላ አገልግሎት ሂደት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ወስጥ ማስገባት አለባቸው።

10. ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 12 61 57 67 በመደወል መረዳት ይችላሉ።

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገፈርሳ ጉጂ ክፍለ

ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender