በሀድያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች ሥራ አገልግሎት የሚውል ጽ/መሣሪያ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀድያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር አለወፋ/ጽ/መ/ግዥ/01/2018
በሀድያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች ሥራ አገልግሎት የሚውል ጽ/መሣሪያ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ያላቸው እና የዕቃ አቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሀገር አቀፍ ጨረታ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከአንሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነድ ላይ የተመለከተውን አስፈላጊ ዕቃ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በተገለጸው ዝርዝር መግለጫ / ስፔስፊኬሽን መሠረት ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ተለይቶ በመሙላት በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ በመጻፍ ማህተምና ፊርማ በማሳረፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ /የጽሕፈት መሣሪያ/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 4,500 /አራት ሺህ አምስት መቶ ብር/ በባንከ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ካሽ በአንሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱንና የግዥ ውል እንዲፈጽም ከመ/ቤቱ ደብዳቤ በደረሰው ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት የሥራ ቀናት ጊዜ የዕቃ የአቅርቦት ውል ከግዥ ፈጻሚ መ/ቤት ጋር መፈራረም ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራች የውል ስምምነት እንዲፈጽም በተገለጸበት ጊዜ ከአሸነፉበት ዕቃ አገልግሎት ከጠቅላላ ዋጋ 10% የግዥ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
- በአንድ ጊዜ በሚፈጸመው ከ10,000 / አስር ሺህ / ብር በላይ በሆነ ግዥ የአገልግሎት ታክስ 2% የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 በመ/ቤታችን ግዥና አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛ ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡ በጨረታ መክፈቻ ሰዓት ተጫራቾች / ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን መከፈቻ ሥነሥርዓት አያስተጓጉልም፡፡
- አሸናፊ ተጫራች በመጫረቻ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩ ዕቃዎችን ሙሉ በሙሉ በራሱ ወጪ እስከ መ/ቤታችን ድረስ አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462630265 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በሀድያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
