Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
  • Address ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116733497
  • Website
  • Deadline17 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ)
  • opening date2025-11-17 00:00:00
  • Categories Water Pipes And Fittings

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር የ ቧንቧ ዕቃዎች ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EAC 014/2018

 

  1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር የ ቧንቧ ዕቃዎች ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30- 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -11፡00 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር” ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-
  • አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
  • አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
  • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡
  • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
  1. ተጫራቾች የቧንቧ ዕቃዎች ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ተፈጻሚ ይሆናል።
  3. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  4. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116676204 ፋክስ ቁጥር 0116732006 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  5. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር

 

Save Tender