በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር ግዥ በ2018 በጀት አመት ለኮሩ አገልግሎት የሚውሉ ነገሮችን በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚ/ር 6ኛ እዝ 602ኛ ኮር
የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር ግዥ
ግልፅ ጨ/ቁ 01/2018 ዓ/ም
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር ግዥ በ2018 በጀት አመት ለኮሩ አገልግሎት የሚውሉ፡-
- አላቂ የቢሮ ጽህፈት ማቴሪያል
- አላቂ የስልጠናና ትምህርት ማቴሪያል
- ቅስቀሳና ፕሮፖጋንዳ ማቴሪያል
- አላቂ የቢሮ ፅዳት ማቴሪያል
- ቶዮታ 1HZJ 79 መኪና መለዋወጫ
- ኩን ሃይሎከስ 25L መኪና መለዋወጫ
- የጀነሬተር መለዋወጫ
- አላቂ የጋራዥ መኪና እቃዎች
በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በዚህ መሰረት በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋዩ ሰርተፍኬት ያላቸው ፤የምዝገባ የምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ቅዳሜን ጨምሮ ከጠዋቱ ከ2:00-6:00 ሰአት ከሰዓት በኋላ ደግሞ ከ 7:30-11:00 ድረስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ምስ/ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የትኖራ ቀበሌ የ602ኛ ኮር ግዥ ክፍል ጊዜያዊ ቢሮ በመቅረብ እስከ ህዳር 13/03/2018 ዓ/ም የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ህዳር 13/03/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 04 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4:30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ምስ/ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የትኖራ ቀበሌ የ602ኛ ኮር ግዜያዊ ማዘዣ ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0912368899/0926600397
በሀገር መከላከያ ሚ/ር 6ኛ እዝ 602ኛ ኮር
