የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀጽ 9 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚፈለግባቸውን የታክስ ዕዳ በሕግ በተቀመጠው ጊዜ ባለመክፈላቸው ምክንያት በሶስተኛ ዙር የግልፅ ጨረታ አውጥቷል።
Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)
የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀጽ 9 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚፈለግባቸውን የታክስ ዕዳ በሕግ በተቀመጠው ጊዜ ባለመክፈላቸው ምክንያት በሶስተኛ ዙር የግልፅ ጨረታ በማውጣት ከዚህ በታች የተገለፁት ቤቶች ማለትም ንብረትነታቸው፡-
- የአቶ ኤልያስ ብርሀኔ ገ/ማርያም ሀብት (ንብረት) የሆነውን ባለ ሁለት መኝታ ቤት ኮንዶሚንየም (ለአራተኛ ጊዜ ለጨረታ የቀረበ)፣
- የአቶ ፍቅረስላሴ አለማየሁ መድህን ሀብት (ንብረት)የሆነው ለመኖሪያ ቤት የሚያገለግል ጅምር ቤት (ለመጀመሪያ ጊዜ ለጨረታ የቀረበ)፣
- የአቶ ሀይለ ግደይ ተሰማ ሀብት (ንብረት) የሆነውን የባህል አዳራሽ (ለመጀመሪያ ጊዜ ለጨረታ የቀረበ) እና
- የአቶ ፀጋዬ ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሔር ሀብት (ንብረት) የሆነውን ባለሶስት መኝታ ቤት ኮንዶሚንየም (ለመጀመሪያ ጊዜ ለጨረታ የቀረበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከላይ የተጠቀሱትን ቤቶች (ሀብቶች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ቢሮው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ሠነድ በመግዛት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡-
- ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተወዳዳሪ ቤቶችን ለመግዛት ወይም ለመጫረት ነጋዴ ከሆነ፣ የወቅቱን የ2017 የግብር ዘመን የሚጠበቅበትን የግብር/ታክስ ግዴታ የተወጣ ወይም የከፈለ እና ለዚህ ማስረጃነትም ከሚመለከተው ገቢ ሰብሰቢ መ/ቤት የተሰጠ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችል፣በተጨማሪም ማንነትን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ፣ የታደሰ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ማቅረብና እና ሌሎች ለዚሁ ጨረታ እንደመስፈርት የተቀመጡትን መስፈርቶች ሁሉ መሟላት አለበት።
- ቤቶቹን ለመጫረት የእያንዳንዱ እና ጠቅላላ የንብረቶቹ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት በጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ እና በጨረታ ሠነዱ ላይ በአባሪ 01 /አንድ/ ተያይዞ በቀረበው ሠንጠረዥ ዝርዝር መረጃ መረዳት የሚቻል ሲሆን የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 500 ብር (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል አፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት ከአማጋ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመግዛት የንብረቶቹ መረጃ እና ስለንብረቶቹ ዝርዝር መመሪያዎች መመልከት ይችላሉ፡፡
- ስለ ቤቶቹ አሻሻጥና ዝርዝር መረጃ በተመለከተ በታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ስር የሚገኘውን በታክስ ዕዳ የተያዙ ንብረቶች አስተዳደር እና ሽያጭ ቡድን አፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ 3ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ (ዋስትና) ለእያንዳንዱን የጨረታ መነሻ ግምት የተሠራላቸው ቤቶች በጨረታ ሠነዱ ላይ እና በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በተመላከተው የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) Addis Ababa city government Revenues Bureaue" ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ቤቶቹ (ንብረቶቹን) የሚገዙበት ዋጋ በግልጽ ሁኔታ በማስፈር በሰም በታሸገ ካኪ ፖስታ (በታሸገ ፖስታ) አሽገው አድራሻ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ብሎ በመፃፍ ይህ የቤቶች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን እስከ 31ኛው ቀን ወይም የመጨረሻው ቀን በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ31ኛው ቀን ወይም የመጨረሻው ቀን በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ የጨረታ ዋጋቸውን 3ኛ ፎቅ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- የቤቶቹ የግልጽ ጨረታው በ31ኛው ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ወይም የመጨረሻው ቀን በበዓል ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ወይም የመጨረሻው ቀን በበዓል ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት 2018 ዓ.ም በቢሮው መሰብሰቢያ አዳራሽ 3ኛ ፎቅ ይከፈታል።
- የግልጽ ጨረታ አሸናፊው ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲ.ፒ.ኦ እና ሌላ ተጨማሪ የውል ማስከበሪያ ለንብረቱ በሰጡት ዋጋ ላይ የሚሰላ 10% እና ያሸነፋበትን ሙሉ ዋጋ ቢሮው በሚያሳውቀው የባንክ ሒሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የባንክ ገቢ ደረሰኝ ለቡድኑ ዋናውን አሳይቶ ኮፒ ደረሰኝ በመስጠት እና የቢሮው የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈል ቤቱን (ንብረቱን) መረከብ አለበት እንዲሁም ለጨረታ ተሸናፊዎች በአምስት ቀናት ውስጥ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱን ይሰረዛል፡፡
- ቢሮው ስለ ንብረቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉም የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
|
የመኖሪያ ቤቱ መለያ ኮድ |
የግብር/ታክስ ባለዕዳው ስም |
ቤቱ የሚገኝበት ክ/ከተማ |
ወረዳ |
የቤቱ ስፋት |
የቤቱ የአገልግሎት ዓይነት |
የሚገኝበት ልዩ ቦታ |
የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ |
በተጫራቹ የተሰጠ የቤቱ የጨረታ ዋጋ |
ምርመራ |
|
|
በተጫራቾች የቀረበ የአንዱ ዋጋ በአሀዝ |
ለቤቱ በተጫራቾች የቀረበ የአንዱ ዋጋ በፊደል |
|||||||||
|
001 |
አቶ ኤልያስ ብርሀኔ ገ/ማርያም |
ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ |
ወረዳ 03 |
55.42 ካ/ሜ |
መኖሪያ ቤት |
ግራር ኮንዶሚንየም |
2,138,883.70 |
|
|
|
|
002 |
አቶ ፍቅረስላሴ አለማየሁ መድህን |
አቃቂ ቃሊቲ |
ወረዳ 13 |
94.64 ካ/ሜ |
ለመኖሪያነት የሚያገለግል ጅምር ላይ ያለ ቤት |
አለም ባንክ |
4,350,826.64 |
|
|
|
|
003 |
አቶ ሀይለ ግደይ ተሰማ |
ቦሌ |
ወረዳ 04 |
307 ካ/ሜ |
የባህል አዳራሽ |
ቦሌ 22 አዲስ ሕይወት ሆስፒታል ጀርባ |
22,747,477.00 |
|
|
|
|
004 |
አቶ ፀጋዬ ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሔር |
ለሚ ኩራ |
ወረዳ 14 |
103.36 ካ/ሜ |
ኮንዶሚንየም |
የካ አባዶ |
3,531,721.78 |
|
|
|
|
|
አጠቃላይ ድምር 32,768,909.12 |
|
|
|
||||||
ስልክ ቁጥር +251-011-557-65-42
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በታክስ ዕዳ የተያዙ ንብረቶች አስተዳደር እና ሽያጭ ቡድን
