Tender Detail

Tender Details

  • Company የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንትርፕራይዝ
  • Address ጎንደር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0908085555
  • Website
  • Deadline27 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋውን 1%
  • opening date2025-11-27 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ በ2018 ዓ.ም በተፈቀደ መደበኛ በጀት የዱቄት እና የዘይት ፋብሪካ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንትርፕራይዝ


 

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 የግዥ መለያ ቁጥር E/M/T/C/NCB/02/2018

 

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ በ2018 ዓ.ም በተፈቀደ መደበኛ በጀት የዱቄት እና የዘይት ፋብሪካ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፉ የወጣና ለዘመኑ የንግድ ስራ ፈቃድ ኮፒ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ኮፒ፣ በማንኛውም የመንግሥት ግዥ ጨረታ እንዲሳተፉ በሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የተሰጠ ድጋፍ ደብዳቤ ኮፒ ፈርመውና በድርጅታቸው ማህተም አረጋግጠው ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።
  2. ማንኛውም፣ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 1% ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ ሲፒአ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በእቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ስም አሠርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ90 ቀን በታች መሆን የለበትም፡፡
  3. ተጫራቾች በተ.ቁ 1 እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ እንዲሁም የዋጋ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሻልና ቴክኒካል በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግና በማያሻማ ሁኔታ በጀርባው ላይ ፋይናንሻልና ቴክኒካል፣ ኦርጅናልና ኮፒ በሚል ቃል በጽሑፍ በማመላከትና በድርጅታቸው ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ሁሉም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ተጠቃለው ታሽገውና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጠው መግባት አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስና አስተዳደር ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 06 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዳቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታውም ታዛቢዎችና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት 4፡01 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ይከፈታል፡፡

 

እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ

 

Save Tender