Tender Detail

Tender Details


የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ እያስገባው ላለው ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G+10 ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል የአልሙኒየም አቅርቦትና ስራ፣ የኤሌክትሮ መካኒክ አቅርቦትና ገጠማ፣ የኮርኔስ አቅርቦትና ስራ እና የሸንት ቤት ፓርቲሽን መስኮት አቅርቦትና ገጠማ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰ

Menkorer Construction Enterprize (የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)


ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ እያስገባው ላለው ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G+10 ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል የአልሙኒየም አቅርቦትና ስራ፣ የኤሌክትሮ መካኒክ አቅርቦትና ገጠማ፣ የኮርኔስ አቅርቦትና ስራ እና የሽንት ቤት ፓርቲሽን መስኮት አቅርቦትና ገጠማ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

•        ምድብ 1 ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G+10 የአልሙኒየም አቅርቦትና ስራ

•        ምድብ 2 ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G+10 የኤሌክትሮ መካኒክ አቅርቦትና ገጠማ

•        ምድብ 3 ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G+10 የኮርኔስ አቅርቦትና ስራ

•        ምድብ 4 ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G+10 የሸንት ቤት ፓርቲሽን መስኮት አቅርቦትና ገጠማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1)     ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ሰነድ ያንዱን ዋጋ በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ማስገባት አለባችሁ፡፡

2)     ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በበአላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመክፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡

3)     ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የገበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡

4)     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 እና አዲስ አበባ 4ኪሎ አልማ ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ሆኖም የጨረታ ፖስታው ገቢ የሚሆነው ደ/ማርቆስ ከተማ ድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ነው።

5)     በየምድባቸው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6)     በምድ 2 ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።

7)     በምድ 2 ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የመልካም ስራ አፈጻጸም አንድ እና ከዚያ በላይ የሰሩበትን ማቅረብ አለባቸው፡፡

8)     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ የጠ/ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9)     አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ የመድን ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡

10)                        አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በየምድቡ የተዘረዘሩትን በራሱ ትራንስፖርት በየፕሮጀክቱ ወስዶ በማቅረብ ማስረከብ አለበት፡፡

11)                        አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በየምድቡ የተዘረዘሩትን በራሱ ትራንስፖርት በየፕሮጀክቱ በማቅረብ ሰርቶ ማስረከብ አለበት፡፡

12)                        አሸናፊው ድርጅት ምድብ 1 እና ምድብ 2 ላይ ያሉትን በተያያዘው ድሮይንግ መሰረት ሰርቶ ማስረከብ አለበት፡፡

13)                        አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው እቃዎች አቅርቦትና ስራ በባለሙያ ተረጋግጦ ማለፍ አለበት፡፡

14)                        አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል፡፡

15)                        ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ባሉት 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡

16)                        ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0920514407 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በደ/ማርቆስ ከተማ/አስተዳደር መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት

Save Tender