Tender Detail

Tender Details


በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ 112ኛ ኮማንዶ ከፍለ ጦር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ 112ኛ ኮማንዶ ከፍለ ጦር


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መሰያ ቁጥር የኮ/ክ/ጦር ግ.ጨ 01/2018

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ 112ኛ ኮማንዶ ከፍለ ጦር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት እንድ :- አላቂ የፅህፈት ዕቃዎች እና የስልጠና ማቴሪያሎች

ሎት ሁለት : አላቂ የቢሮ ዕዳት ዕቃዎች እና የህሙማን ማገገሚያ

ሎት ሦስት : ሉቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች

ሎት አራት ፡- ስልጠና ማቴሪያሎች፣ የህንፃ መሳሪያዎች እና ለወታደራዊ ተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች፦

1. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ በዘርፉ ቀጥተኛ ተዛማጅ ያለው በዘመኑ የታደስ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብርከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) የምስከር ወረቀት እና የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚ/ር በወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን/ የዕቃ አቅራቢነት ምስከር ወረቀት/ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የሚውል ገንዘብ ለእያንዳንዱን ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንት ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለባቸው፡፡

3. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለአንድ ሎት በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን ውስጥ ባሉት የስራ ቀናት ወንዶ ጢቃ ማለትም ከጥቁር ውሃ ወደ ሀዋሳ ኤርፖርት በሚወስደው መንገድ 8 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ካምፕ ፋይናንስ ዴስክ ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 01/03/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 17/03/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ግዢ ዴስክ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው 18/3/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ በግዥ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡

6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ስተጨማሪ ማብራሪያ 09-84-78-56-66/ 09-10-31-80-43 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅሳደ መምሪያ 112ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር

Save Tender