የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን የተባለ የበጐ አድራጐት ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የጽ/ቤት እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Federation of Ethiopian Associations of Persons with Disabilities (የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን) (ኢ.አ.ጉ.ማ.ፌ)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን የተባለ የበጐ አድራጐት ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የጽ/ቤት እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የቤ.ቁ 1057 የኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ መግቢያ ፊት ለፊት በሚገነጠለው አስፋልት እንቁ ስላሴ ጐዳና 70 ሜትር አካባቢ ገባ ብሎ በሚገኘው ጽ/ቤታችን ከጠዋቱ 3፡00- 10:00 ሠዓት ድረስ በአካል ቀርቦ የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) አሰርተው ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በዳሽን ባንክ ወይም በአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ከ5 የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚሸጡትን ንብረቶች መረጃ የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝ እና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ በፌዴሬሽናችን ጽ/ቤት በመቅረብ በአስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገርግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጐኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሠነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ገንዘቡን ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው። ይህ ካልሆነ በሲፒኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዙት ጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጐ ሁለተኛው አሸናፊ ራሱ ባሸነፈበት ዋጋ ከፍሎ እንዲገዛ ይደረጋል፡፡
- ተጫራች የድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ጋር በመቅረብ የንብረቶቹን ሙሉ መረጃ የያዘ ሠነድ በመግዛት ተጫራቾች የጨረታውን መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከ6ኛ ቀን እስከ 10ኛው ቀን ደግሞ ንብረቶቹ በአካል የሚታዩበት ሲሆን በ10ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ጨረታው ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1553003 / 0921-324330/
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን (ኢ.አ.ጉ.ማ.ፌ.)
