ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የወርክ ሾፕ ዕቃዎች፣ ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር EAC 011/2018
1.ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የወርክ ሾፕ ዕቃዎች፣ ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 - 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -11፡00 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው ኢትዮ አግሪ ሴፍትሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታከስ ከሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት
* አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
* አንድ ቅጂ/Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
* ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡
* በዋናውና የቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች የወርክ ሾፕ ዕቃዎች ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ከፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመከፈቻ ቀን ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ተፈጻሚ ይሆናል::
5. ከላይ የተገለጻ መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሰረዝ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116676204 ፋክስ ቁጥር0116732006 መጠቀም ይችላሉ፡፡
8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር
