Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Regional State Transport and Road Development Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)
  • Address ዲላ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461316004
  • Website
  • Deadline25 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price50.00
  • Bid Securityከጠቅላላ ዋጋ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ)
  • opening date2025-11-25 00:00:00
  • Categories Stationery Materials

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የተለያዩ የጽህፈት ዕቃዎች ማለትም ወረቀት፣ እስክርቢቶ፣ ባለብረት አቃፊ፣ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

South Ethiopia Regional State Transport and Road Development Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)


 

የጽህፈት ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 15/2018

 

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የተለያዩ የጽህፈት ዕቃዎች ማለትም ወረቀት፣ እስክርቢቶ፣ ባለብረት አቃፊ፣ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ዓመታዊ የስራ ግብር የከፈለበትን፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ጨረታ ሰነድ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝር አስፔስፍኬሽንና የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ መጥተው የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 11:30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4:30 ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ወይም ባንክ ጋራንቲ በቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሻል አንድ ኦርጀናልና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በእናት ፖስታ ታሽጎ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሳያስገቡ ለጨረታ ካስገቡት ዕቃዎች ውስጥ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዓይነት አንዳንድ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
  7. ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የደቡብ /ኢ/ክ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ እንደገና ተሻሽሎ የወጣው የግዢ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና መመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሰርኩላር ተፈጻሚ ይደረጋል።

ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 131 60 04 መደወል ይችላሉ።

አድራሻ ዲላ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ

 

Save Tender