Tender Detail

Tender Details


በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የመንገድ ጥገና ግንባታ በደረጃ 10 እና በላይ RC/GC ዘርፍ፣ ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ውሃ እቃዎችና የተሸከርካሪ ቅባትና ዘይቶችን፣ የተለያዩ ብረታ ብረቶችና አሮጌ የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን እንዲሁም የተሽከርካሪ ጥግ ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ይጋበዛል፡፡

በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የመንገድ ጥገና ግንባታ በደረጃ 10 እና በላይ RC/GC ዘርፍ፣ ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ውሃ እቃዎችና የተሸከርካሪ ቅባትና ዘይቶችን፣ የተለያዩ ብረታ ብረቶችና አሮጌ የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን እንዲሁም የተሽከርካሪ ጥግ ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ይጋበዛል፡፡

  • በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው /ያላት!
  • በዘርፉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው /ያላት!!
  • በሎት 1: እና 6 ላይ የሚወዳደሩ ከሆነ በዘመኑ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው!
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት ትክክለኛ ሲፒአ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ/መሂ-1/፡-ማስያዝ አለባቸው

ሎት

የጨረታው ዓይነት

የጨረታ ሰነድ መሸጯ ዋጋ

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

1

የመንገድ ጥገና ግንባታ

200

60,000

2

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

200

15,000

3

የውሃ እቃዎች

200

30,000

4

የተሸከርካሪ ቅባትና ዘይት

100

6,000

5

የብረታ ብረትና አሮጌ የውሃ መሳቢያ ፓምፕ

100

10,000

6

የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት

100

5,000

  • ሎት 1 ላይ የሚወዳደሩት የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ከሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እና አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ ከአደራጃቸው አካል በደብዳቤ ዋስትና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ የማይመለስ ብር በመክፈል ከሲ/ዋዩ ወ/ገን/ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ሎት 1 የተገለፀው ጨረታ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቶች ክፍት ሆኖ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል ፡፡
  • ከሎት 1: በስተቀር ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቶች ከፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል ፡፡

 

  • ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ካለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት ኦርጅናሉን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፖስታው ላይ ስማቸውን፣ አድራሻቸውን እና የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዓይነት በመፃፍ ሲያ/ዋ/ወገን/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው አስገሚዘጋበት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ወጪ በማጓጓዝ በዮፑሉ በሚገኙ ንብረት ከፍሎች ገቢ ያደርጋል፡፡
  • አሸናፊ ተጫራቶች አሸናፊነታቸው በማሰታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ከተጨማሪ እሴተ ታከስ ጋር በባንክ በተመሰከረ ትከከለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ /መሂ-1/ በማስያዝ ውል ይፈፅማል፡፡
  • በሎት 2 ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የእቃዎችን ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • በሎት 6 ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ደረጃ ሁለት እና በላይ የሆኑ እና እሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ካሎት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 3% ከተጨማሪ እሴት ታከስ ጋር በባንክ በተመሰከረ ትከከለኛ ሲፒአ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ /መሂ-1/ በማስያዝ ውል ይፈፅማል፡፡
  • ሎት 5 ላይ አሸናፊ የሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 ተከታታይየስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለገንዘብ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ዕቃዎቹን መውሰድ አለበት፡፡
  • መ/ቤቱ በግዥው ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  • የጨረታ ውድድሩ በጥቅል ዋጋ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
  • መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116200679 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ ፡- በሎት 5 ላይ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በመግዛትና የጨረታ ማስከበሪያውን በማስያዝ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender