የአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት በ2018ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
የአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት
የግዢ ጨረታ ማስታወቂ ቁጥር 0001/2018
የአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት በ2018ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ማለትም :-
- ሎት1 የደንብ ልብሶች
- ሎት2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት3 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- ሎት4 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት5 ልዩ ልዩ መሣርያዎች
- ሎት6 ቋሚ እቃዎችን
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-
2. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው::
3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ስም በባንከ ሲፒኦ (CPO) ለእያንደንዱ ለሚሳተፍበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
6 ይህ ጨረታ ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ብቻ ነው::
7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አቃቂ ብሩህ ተስፈ የመ/ደ/ት ቤት በሂሳብ ቁጥር 1000014692731 ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በማስገባት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20 በፋያናንስ በማወራረድ በትምህርት ቤቱ ግዠ እና ንብረት አስተዳደ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም ፣ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-11፡30 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
9. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ ከታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
|
1 |
ሎት -1- የደንብ ልብስ |
30,000 |
|
2 |
ሎት 2- አላቂ የቢሮ እቃዎች |
15,000 |
|
3 |
ሎት 3 አላቂ የትምርት እቃዎች |
17,000
|
|
4 |
ሎት -4- አላቂ የፅዳት እቃዎች |
30,000 |
|
5 |
ሎት 5 ልዩልዩ መሰሪዎች |
5,000 |
|
6 |
ሎት -6 ቋሚ እቃዎች |
20,000 |
10. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበርያ ማስያዝ ይኖርቦታል፡፡
12. ጨረታውን ለማባዛት የሚሞከር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበርያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው፡፡
13. በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች ለሚያመርቱት ምርት ብቻ ከከፍያ ነፃ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማፃፍ እና ለማያመርቱት ምርት (ዕቃ/ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛት እና በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
14. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 በትምህርት ቤቱ በፋይናስ ቡድን መሪ ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 22 ይከፈታል፡፡
15. መስርያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
16. ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- 011-4-71-55 09/011-4-71-62-92/3/011-4-34-30-96 አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ከወረዳ ሁለት ፊት ለፊት በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ወደውስጥ ገባ ብሎ አቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤ
የአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት
