Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ
  • Address ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0577752979
  • Website
  • Deadline24 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-11-24 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ 2018 በጀት ዓመት ከመደበኛ በተገኘ በጀት የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ሰርተፍኬት ህትመት የሀገር በቀል ሶፍትዌርን በመጠቀም ለመመዝገብና ፈተናውን ለማረም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች ቁሳቁች ማለትም Datasheet image Scanner/ የፈተና ማረሚያ ማሽን/፣ Printer /ፕሪንተር/ and Smart Security lp Camera /የደህንነት ካሜራ! በስራ ዝርዝራቸው ወይም ስፔስፍኬሽን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ 2018 በጀት ዓመት ከመደበኛ በተገኘ በጀት የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ሰርተፍኬት ህትመት የሀገር በቀል ሶፍትዌርን በመጠቀም ለመመዝገብና ፈተናውን ለማረም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች ቁሳቁች ማለትም Datasheet image Scanner/ የፈተና ማረሚያ ማሽን/፣ Printer /ፕሪንተር/ and Smart Security lp Camera /የደህንነት ካሜራ! በስራ ዝርዝራቸው ወይም ስፔስፍኬሽን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በዘርፉ መወዳዳር የሚችሉ መሆኑ ይጋብዛል፡፡

1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የማስረጃዎቹን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. የዕቃዎቹን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነዱን ብር 200 በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከልል መንግስት ት/ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳዳር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ማግኘት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር 2% /ሁለት ፐርሰንት /ብቻ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO/ሲ.ፒ.አ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ወይም ጥሬ ገንዘብ ከዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በግልጽ የመወዳደሪያ ሠነዶቻቸውን ኦርጅናሉንና ፎቶ ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ኛው ተከታታይ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ሰዓት ላይይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡

7. አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን 1% በማስያዝ ማሸነፋቸው ከተገለጽላቸዉ በ7 ቀናት ውስጥ ውል ባይገቡ ለጨረታ ያስያዙት 2% ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

8. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡበት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. አሸናፊው ተጫራች የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ሰርተፍኬት ህትመት የሀገር በቀል ሶፍትዌርን በመጠቀም ለመመዝገብና ፈተናውን ለማረም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኤሌከትሮኒክሶች ቁሳቁች ማለትም Datasheet Image Scanner/ የፈተና ማረሚያ ማሽን/፣ Printer /ፕሪንተር/ and Smart Se-curity Ip Camera / የደህንነት ካሜራ/ ግዥ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ከልል መንግስት ት/ቢሮ መጋዘን ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማስረከብ አለበት::

11. ተጫራቾች በጨረታው መከፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባይገኙ የጨረታውን ሂደት አያስተጓጎልም፡፡

ስበስጠ መረጃ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ የግዥ/ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በስልክ ቁጥር 0577752979 መጠየቅ ይችላሉ ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ

Save Tender