Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ
  • Address በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፣ኢትዮጲያ, Phone: 046 554 1977
  • Website
  • Deadline24 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-11-24 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Stationery Materials

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ፖሊቲን ትዩብ ፣ የእስቴሽነሪ እና ጽዳት ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 10/2018

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ፖሊቲን ትዩብ ፣ የእስቴሽነሪ እና ጽዳት ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፦

ተ/ቁ

የዕቃው ዓይነት

መለኪያው

ምርመራ

1

ሎት አንድ ፡- የፖሊቲን ትዩብ ግዥ

በኪ/ግ

የሁሉንም ሎት ዕቃዎች ብዛት እና ዓይነት ዝርዝር መረጃ በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል

2

ሎት ሁለት ፡-የእስቴሽነሪ ግዥ

በቁጥር

3

ሎት ሶስት - የጽዳት እቃ ግዥ

በቁጥር

 

  • ተጫራቾች የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት አግባብ ያለው በኦን ላይን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስከር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስከር ወረቀት፣የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ የምስከርወረቀት፣ እና ሌሎች ያሏቸውን ማስረጃዎቻቸውን በግልጽ ሊነበብ በሚችል መልኩ አደራጅተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዱራሜ ከተማ ከቀድሞ ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ርቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይቻላል።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ /ፕሮፎርማ/ ፋይናንሻል ዶከመንት ኦርጅናል በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ/ፋ/ንብ/አሰ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ ፡፡
  • ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡
  • መ/ቤቱ ከጠቅላላው የግዥ መጠን (ብዛት) ላይ ከውል በፊት 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • ከዚህ በፊት በጥፋተኝነት ከፌዴራል እስከ ተለያዩ ከልሎች በግዥ ሂደት ላይ የጥፋተኝነት ሪፖርት ቀርቦባቸው በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ያልታገዱት ብቻ በጨረታው መወዳደር/መሳተፍ የሚችሉ ይሆናል ፡፡

ለለበጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 554 1977 ዘወትር በሥራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ             

Save Tender