የኤግዚብሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የቤትና የቢሮ እቃዎች መገልገያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
EXHIBITION CENTER & MARKET DEVELOPMENT ENTERPRISE (የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት)
ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት
EXHIBITION CENTER & MARKET DEVELOPMENT ENTERPRISE
የቤትና የቢሮ እቃዎች መገልገያዎች ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የኤግዚብሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የቤትና የቢሮ እቃዎች መገልገያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የቤት እቃዎች መገልገያዎች
- ሎት 2 የቢሮ እቃዎች መገልገያዎች
- ሎት 3 የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችና ተዛማጅ እቃዎች
- ሎት 4 ኮምፒተርና ላፕቶፕ እና ተዛማጅ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ስለሆነም
- የታደስ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ማንኛውም የእቃ ግዥ ለአገልግሎት 3 በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል
- የእቃውን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ Exhibition Center & Market Development Enterprise በሚል አድራሻ በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱን ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን 500 ብር በመክፈል ከኤግዚብሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ እና ቲን ነምበር በአንድ በታሸገ ፖስታ ኦርጂናል የጨረታ ሰነድ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጂናል ብለው በመፃፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 14 ቀን 2018 ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ15ኛው ቀን ህዳር 15 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡10 ሰአት የኤግዚብሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት መ/ቤት ተጫራቾችና እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- በጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ነገርግን ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115151693 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
ኤግዚብሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት
