Tender Detail

Tender Details

  • Company BUNNA INSURANCE S.C (ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት ጀርባ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-126-31-03
  • Websitehttps://www.bunnainsurance.com/
  • Deadline01 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-12-01 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ለተጎዱ ተሸከርካሪዎች እና ንብረቶች ማቆያ ቦታ (Recovery Yard) አገልግሎት የሚውል ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

BUNNA INSURANCE S.C (ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ)


 

ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ.

BUNNA INSURANCE S.C.

 

የተጎዱ ተሽከርካሪዎች እና ንብረቶች ማቆያ ቦታ (Recovery Yard) ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

 

  • ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ለተጎዱ ተሸከርካሪዎች እና ንብረቶች ማቆያ ቦታ (Recovery Yard) አገልግሎት የሚውል ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ የመሬት ባለቤቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለ ክፍያ በመውሰድ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች እና ሰነዶች በመሟላት በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ኩባንያችን ይጋብዛል።

ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ግዥ መፈፀም የሚፈልገው ቦታ ዝርዝር ሁኔታዎች፡

    1. ህጋዊ ዲጂታል ካርታ ያለው
    2. ቦታው ከ5000ካ.ሜ እስከ 7000ካ.ሜ የሆነ
    3. ወቅታዊ ግብር የተከፈለበት
    4. የባለቤትነት ይዞታው በሊዝ ወይም በምሪት የሆነ
    5. ቦታው የድርጅት ወይም የግለሰብ (የግለሰብ ከአንድ በላይ ከሆኑ የሁሉም ወራሽነት ወይንም ህጋዊ ውክልና) ያለው
    6. እግድና እዳ የሌለበት
    7. የአካባቢ LDP/Local Digital Plan/ መንገድ የማይነካው
    8. የከባድ መኪና ጋራዦች በቅርብ ርቀት የሚገኝበት
    9. ምስራቅ አዲስ አበባ መውጫ (ለቡ፣ ንፋስ ስልክ፣ አቃቂ ቃሊቲ...) አካባቢ
    10. ቦታው ለስራ አመቺ (Access Road) ያለው
    11. ትላልቅ መኪኖች፤ ክሬኖች፤ ሎቤድ ወዘተ ሲዞሩ /ለመግባትና ለመውጣት/ የማያስቸግር አካባቢ
    12. በውስጥ ግንባታ ካለው ግንባታው የተፈቀደበት እና ብሉፕሪንት ያለው
    13. ቦታው ባልተጋነነ ወጪ ወዲያውኑ ለአገልግሎት የሚውል
  • ይህ የቦታ ግዥ ጨረታ ለ22 ተከታታይ ቀናት ከጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው ሰኞ ህዳር 22 ቀን 2018ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 4፡30 ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ መሰብሰቢያ አዳራሽ (ምድር ቤት) ይከፈታል።
  • ተጫራቾች የቴክኒክ መወዳደሪያ ሀሳብና የፋይናንስ ዋጋ ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፓስታ (ኢንቨሎፕ) በጨረታ ሰነዱ በተመለከተው መሰረት በሚከተለው አድራሻ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስታወቂያ ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል

የስልክ ቁጥር፡- 011-4-70-59-08/011-1-26-31-03

አዲስ አበባ

 

Save Tender