Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር
  • Address በካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 0476680500
  • Website
  • Deadline08 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price800.00
  • Bid Security200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-08 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ/ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል።

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2018

 

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ/ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች/ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. የ VAT ተመዝጋቢ፣ TIN ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በመ/መ/ቤት አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ደረጃ 5 BC/GC እና ከዚያ በላይ የስራ ፈቃድ ማቅረብ የምትችልና የስራ ፍቃዱ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስተር እና በክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ህጋዊ ማረጋገጫ የተሰጠው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ሆኖ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 800/ ስምንት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከሺሸንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ/ ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ላይ ዘወትር በሥራ ሠዓት የድርጅታቸውን ዶክመንት ኮፒ ይዘው በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ኦርጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል ከሁለት ሁለት ኮፒዎች ጋር ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ/ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  3. እያንዳንዱ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት ከስራ ፍቃዳቸው ውጭ መወዳደር እና የሌላውን ተወዳዳሪ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም።
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ/ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው። ጨረታ በ31ኛ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል 33ኛ ቀን ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን (CPO) ለተሸናፊው ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስከ 7ኛው ቀን ድረስ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  7. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

 

ማሳሰቢያ ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0476680500/0917950945 በመደወል መረዳት ይቻላል።

 

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር

 

Save Tender