አሰፋ መስማት የተሳናቸው 2ኛ ልዩ /ት/ቤት በሀገር ውስጥ ለሚፈጸሙ እቃዎችና ተዛማጅ አገልግሎቶች የሚውል የሚገዙ እቃዎች:- የአላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ የህከምና እቃዎች፣ የላብራቶሪ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ቦሌ ክፍለ ከተማ አስፋ መስማት የተሳናቸው 2ኛ ልዩ /ት/ቤት
የጨረታ ማስታውቂያ
በጨረታ ስሚገዙ ዕቃዎች ስተጫራቾች የ2ኛ ዙር
የጨረታ መመሪያ ሰነድ የጨረታ ቁጥር 02/2018
በሀገር ውስጥ ለሚፈጸሙ እቃዎችና ተዛማጅ አገልግሎቶች የሚውል የሚገዙ እቃዎች:- የአላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ የህከምና እቃዎች፣ የላብራቶሪ እቃዎች
- በመጀመረያ ደረጃ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የሚችሉት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዝጋቢ የምስከር ወረቀት ያላቸው ወይንም ማቅረብ የሚችሉ ብቻ ናቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሂሳብ የዕቃው አይነት የተመረተበት ዓመተ ምህረት የአገልግሎት ዘመን ማብቂያ የአምራቹ ስም ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በየዘርፉ ንግድ ፈቃድ መኖር አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቶች ዋናው የጨረታ ሰነድ ላይ በተጫራቹ የሚሞሉትን በመሙላት እያንዳንዱ ገጽ ላይየድርጅቱን ማህተም በማኖር ሳይጨምር ና ሳይቀንስ መመለስ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ፖስታ ዋናና ኮፒ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡ እነዚህም ሰነዶች የጨረታ አቅራቢው ድርጅት ወይም ህጋዊ ውክልና ባለው አካል መፈረም አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎች ናሙና ከየአይነቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኃላ የቀረቡት ናሙናዎች ለተሸናፊዎች ሲመለሱ የአሸናፈው ተጫራቾች ግን ናሙናዎች አይመለስም አንድ ተብሎ ይቆጠርለታል፡፡
- ግዢ ፈፃሚው አካል አሸናፊ ተጫራቾች በሚመረጡበት ጊዜ የገዛውን እቃ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነሰ ወይም ለመጨመር ይችላል፡፡
- የመልካም አፈጻጸም ደብደቤ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ፡፡
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈሎ የሚያሳይ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ብቻ፡፡
- የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-11፡00 ይሆናል፡፡ ይህ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ እስከ ለ10/አስር/ የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል፡ በ10ኛው ቀን 9፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሂሳብ ወይም ሰነድ ላይ ሰማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን እንዲሁም ሰልከ ቁጥራቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ የማብራሪያ ወይም ማሻሻል አለበት የሚሉ ጥያቄ ካላቸው የጨረታ ሰነዱ የመከፈቻ ጊዜ ሁለት ቀናት አስከሚቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ግዥ ፈፃሚ አካል ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሰነዱ መሸጫ ዋጋ 100/መቶ/ ብር ብቻ ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ባስገባው ጨረታ ሲፒኦ ማስያዣ ዋጋ ሎት 1፡8000 ለኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ሎት 2፡ 6000 ለፈርኒቸር እቃዎች ሎት3፡3000 ለሌሎች እቃዎች ሎት4፡5000 ለህከምና እቃዎች ሎት 5፡6000 ለላቦራቶሪ እቃዎች ሲሆኑ ሰነዱ በራሱ አንድ የጨረታ መመሪያ መሆኑን ተጫራቾች መረዳት ይኖርባቸዋል
- ከላይ የተዘረዘሩ አንድም ነገር እንኳን የማያሟላ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- የርክክብ ቦታ በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እቃው ለንብረት ከፍል ካስገባና ጥራቱ ከተረጋገጠ በኋላ ከፍያው ይፈጸማል፡፡
አድራሻ፡- አልፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ስሙ ከኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ነው፡፡
ቦሌ ክፍለ ከተማ አሰፋ መስማት የተሳናቸው 2ኛ ልዩ /ት/ቤት
