Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
  • Address አሶሳ ፡ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 057 775 2144
  • Website
  • Deadline24 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-11-24 00:00:00
  • Categories Machinery , Other Sales , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሩዝ መፈልፈያ ማሽን እና የፖለቲውን ቲውብ ግዥ በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ

 

  • የሩዝ መፈልፈያ ማሽን ግዥ ጨረታ ቁጥር 08/2018 ዓ/ም
  • የፖለቲውን ቲውብ ግዥ ጨረታ ቁጥር 09/2018 ዓ/ም

ከላይ የተገለፁትን ግዥ ለመፈፀም የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለ2017/18ዓ/ም በዘርፉ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፤ ለ2017/18 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በሀገር ውስጥ ገቢዎች የጨረታ ተሳታፊነት የድጋፍ ደብዳቤ ያለውን የታደሠ የአቅራቢነት ሰርትፊኬት ያላቸውን ተወዳዳሪዎች በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ዝርዝር ጨረታውን የያዘ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል አሶሳ በቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ በግዥ/ብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይቻላሉ፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. አሸናፊ ድርጅት የውል ስምምነት ሲፈርም ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል።
  4. በጨረታው ያልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበረያ የጨረታ አሸናፊ እንደታወቀ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመግዛት እስከ 16ተኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ ነገር ግን ቅዳሜ እሁድ እና የህዝብ በዓል ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘጋል፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሶሳ በሚገኘው በቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ይሆናል፡፡
  8. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

 ለበለጠ መረጃ፡- 0577752144 አሶሳ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ

 

Save Tender