Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa Business Trading Enterprise (የአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ድርጅት)
  • Address ፒያሳ እሪ በከንቱ ኢትዮ ሴራሚክስ ዝቅ ብሎ በሚገኘው EMA TOWER 16ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251942083432
  • Website
  • Deadline24 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2025-11-24 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Food And Beverage

የአዲስ አበባ ንግድ ሥራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የጤፍ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Addis Ababa Business Trading Enterprise (የአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ድርጅት)


 

የሽያጭ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የሽያጭ ጨረታ ቁጥር፡- AABTE/SA/NCB/SG/01/02/2018

 

የአዲስ አበባ ንግድ ሥራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የጤፍ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማመሟት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ
  2. ወቅቱ ያላለፈበት ለጨረታ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስ
  3. ቫት ሰርተፍኬት
  4. የቲን ቁጥር ሰርተፍኬት
  5. በአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ስም የተዘጋጀ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ 500,000 ብር የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል
  6. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከቀን 29/02/2028 ዓ.ም እስከ 14/03/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 14 ቀናት ሆኖ ጨረታው የሚዘጋው በ15ኛው ቀን በ15/03/2018 ዓ.ም 5፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 5፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት EMA TOWER 16ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፣
  7. ተጫራቾች በዚህ ማስታወቂያ የተቀመጡ መስፈርቶችና እና የእያንዳንዱ ኩንታል ጠቅላላ ዋጋ በመግለፅ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ በማዘጋጀት እና በማሸግ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 15ኛው ቀን 5፡00 ድረስ እሪ በከንቱ ከኢትዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ በሚገኘው EMA TOWER 16ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 04 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ገቢ ማድረግ አለባቸው፤
  8. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከተዘረዘሩት የጤፍ አይነቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፤
  9. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉት የጤፍ ዓይነቶች ዝርዝር በጀሞ 1 እና ካራ ኮተቤ ብርሃን የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በሚገኙ መጋዘኖች በስራ ቀናት እና ሰዓት በመገኘት በአካል መመልከት ይችላሉ፤

 

ተ.ቁ

የጤፍ ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

የጤፍ ምርቱ የሚገኝበት መጋዘን

1

ነጭ

ኩንታል

15,184.95

ጀሞ 1 እና ካራ ኮተቤ ብርሃን ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ

2

ሰርገኛ

ኩንታል

12,378.72

ጀሞ 1 እና ካራ ኮተቤ ብርሃን ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ

3

ቀይ

ኩንታል

267.68

ጀሞ 1 እና ካራ ኮተቤ ብርሃን ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ

ድምር

ኩንታል

27,831.62

ጀሞ 1 እና ካራ ኮተቤ ብርሃን ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ

 

  1. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5/አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ለድርጅቱ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል ፡፡ ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  2. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን የጤፍ ዓይነቶች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ከጠቅላላ የኮንትራት ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ንብረቶች በ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው። በተጠቀሰው ቀን ባያነሱ ንብረቱ እና የውል ማስከበሪያው የሚወረስ ይሆናል፡፡
  4. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ድርጅት ፒያሳ እሪ በከንቱ ኢትዮ ሴራሚክስ ዝቅ ብሎ በሚገኘው EMA TOWER 16ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር:- +251942083432/+251987880938

 

የአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ድርጅት

 

Save Tender