በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ወለጋ ዞን የሚገኘው ጊቤ ዲዴሣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ለ2018/19 ምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ህጋዊ የደረቅ ጭነት አጓጓዦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
በምስራቅ ወለጋ ዞን የጊቤ ዲዴሳ ዩኒዬን ጽ/ቤት
ለ2018/19 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ወለጋ ዞን የሚገኘው ጊቤ ዲዴሣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ለ2018/19 ምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ህጋዊ የደረቅ ጭነት አጓጓዦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ መጠን እና ዓይነት።
- ዳፕ = 217,034 ኩንታል
- ዩሪያ = 261,071 ኩንታል
ጠቅላላ ድምር = 478,105 ኩንታል
ሲሆን የአፈር ማዳበሪያ የሚጓጓዝበት ቦታ ከተለያዩ የዩኒዬኑ መጋዘኖች እስከ መሰረታዊ ማህበራት መጋዘን ድረስ ስለሆነ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ወይም ማህበራት ስለ ጨረታው ሰነድ ዝርዝር ከዚህ ጋር በአባሪነት አያይዘን ስላቀረብን ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000001278804 በኦሮሚያ ህ/ሥ/ባንክ ወይም 100001374924 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል አስገብታችሁ የጨረታ ሰነዱን ገዝታችሁ አንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
በዚህ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ሆኖ በአስረኛው ቀን በ11:00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዱን ማስገባት ይኖርበታል፡፡ የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሚቀጥለው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ (በዓል) ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኀብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ጽ/ቤት በምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ስርጭት እና ክትትል ክፍል ይከፈታል፡፡
ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም ወይም በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የምዝገባ ቦታ ፡- በነቀምት ከተማ ጊቤ ዲዴሳ ዩኒዬን ጽ/ቤት ይሆናል።
ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ መረጃ የምትፈልጉ ከሆነ በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይቻላል።
ጊቤ ዲደሣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩንዬን በስልክ ቁጥር 057-661-53-07/0975505059 ወይም በምስራቅ ወለጋ ዞን ህብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ በስልክ ቁጥር 0576616608/ 0917818401
በምስራቅ ወለጋ ዞን የጊቤ ዲዴሳ ዩኒዬን ጽ/ቤት
