በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ወለጋ ዞን የሚገኘው የአንገር አበያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ለ2018/2019 ምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያን ህጋዊ የደረቅ ጭነት አጓጓዦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
የአንገር አበያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን
ለ2018/19 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ወለጋ ዞን የሚገኘው የአንገር አበያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ለ2018/2019 ምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያን ህጋዊ የደረቅ ጭነት አጓጓዦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ መጠን እና ዓይነት፡-
- DAP (ዳፕ)= 83,398 ኩንታል
- UREA (ዩሪያ) = 89,540 ኩንታል
ጠቅላላ ድምር = 172,938 ኩንታል
ሲሆን የአፈር ማዳበሪያ የሚጓጓዝበት ቦታ ከተለያዩ የዩኒዬኑ መጋዘኖች እስከ መሰረታዊ ማህበራት መጋዘን ድረስ ስለሆነ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ወይም ማህበራት ስለ ጨረታው ሰነድ ዝርዝር ከዚህ ጋር በአባሪነት አያይዘን ስላቀረብን ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000016913506 በኦሮሚያ ህ/ሥ/ባንክ ወይም 1000043014912 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በመክፈል ጊቤ ዲዴሣ ዩንየን ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
በዚህ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ሆኖ በአስረኛው ቀን በ11:00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዱን ማስገባት ይኖርበታል። የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሚቀጥው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ (በዓል) ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኀብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጄንሲ ጽ/ቤት በምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ስርጭት እና ክትትል ክፍል ይከፈታል፡፡
ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም ወይም በፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዝገባ ቦታ፡- በነቀምት ከተማ ጊቤ ዲዴሳ ዩኒዬን ጽ/ቤት ይሆናል።
ሞባይል 09 65-02-82-53 ወይም በስልክ ቁጥር 05 77 73 00 19 ወይም በምስራቅ ወለጋ ዞን ህብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ በስልክ ቁጥር 057-661-66-08/09-17-81-84-01
የአንገር አበያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን
