በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በUNDP የበጀት ድጋፍ ለወረዳው ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው ሎት1 ተገጣጣሚ ፈርኒቸር፣ 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና በሴፍቲኔት የበጀት ድጋፍ ሎት1 የአትክልት እና ዘር ግዥ ሎት1 የውሀ መሳቢያ ጀኔሬተሮችን በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የፃ/ወ/ገ/ፅ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በUNDP የበጀት ድጋፍ ለወረዳው ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው ሎት1 ተገጣጣሚ ፈርኒቸር፣ 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና በሴፍቲኔት የበጀት ድጋፍ ሎት1 የአትክልት እና ዘር ግዥ ሎት1 የውሀ መሳቢያ ጀኔሬተሮችን በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን
- ከሚወዳደሩት ስራ ጋር የተዛመደ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer identification Number) ያላቸው፤
- በግዥ አፈጻጸም መመሪያው የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ተመዝጋቢዎች ብቻ እንዲወዳደሩ ከተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች ውጭ የግዥው መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% (አንድ በመቶ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርአት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንክ ዋስትና) ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ /ዋናውን የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን 100 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ፃ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 2003 ተግባራዊ ይደረጋል።
በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የፃ/ወ/ገ/ፅ/ቤት
