Tender Detail

Tender Details


የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ገቢዎች ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የቢሮ ማስዋብ ዕድሳትና ጥገና ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ገቢዎች ቢሮ


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨ/ቁ/001/2018

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት

ሎት አንድ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ሎት ሁለት የቢሮ ማስዋብ ዕድሳትና ጥገና ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት ሥራ ዘርፍ ሎት አንድ የኤሌክትሮኒክስ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የቫት (ተጨማሪ እሴት ታክስ) ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  3. ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 100,000 ብር /አንድ መቶ ሺህ ብር / ከታወቀ ባንክ በሲፒኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ውል ከመፈፀሙ በፊት ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ውል ማስከበሪያ የሚሆን 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ዕቃዎችን እስከ ቦታ ማለትም ሚዛን አማን የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ገቢዎች ቢሮ ንብርት ክፍል ገቢ ማድረግ የሚችል።
  7. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን 1/አንድ/ ኦርጅናል እና 2/ሁለት ኮፒ) በተለያየ በ3 /በሶስት/ ፖስታ በማሸግ በወቅቱ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ ሚዛን አማን ከተማ ገቢዎች ቢሮ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ የሚከፈት ይሆናል።
  9. የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ በፖስታው ላይ እና በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ እንዲያርፍ ይገደዳል።
  10. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ ገቢዎች ቢሮ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
  11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ካልተገኙ የመ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ይህ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ50 ቀናት ይሆናል።

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ገቢዎች ቢሮ

Save Tender