የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓም በመደበኛ በካፒታል በጀት መጽሀፍት ማሳተም እና የመኪና ጋረጅ ጥገና በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Central Ethiopia Region Bureau of Education (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓም በመደበኛ በካፒታል በጀት መጽሀፍት ማሳተም እና የመኪና ጋረጅ ጥገና በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 01 ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍሎች በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጁ እንግሊዘኛ ትምህርት፡ ሂሳብ አጠቃላይ ሳይንስ፣ ማሕበራዊ ሳይንስ፡ የሥነ ዜጋና ስነ ምግባር የመማሪያ መጻሕፍት እትሞ ማሰራጨት ሎት 02 የተሽከርካሪ አመታዊ የጥገና አገልግሎት ግዥ ሎት 03 የፈርኒቸር ሎት 04 የኤሌክትሮኒክስ በመሆኑም ተጫራቾች፦
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያሳደሱ በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት እንደዚሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምሀርት ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት1 ብር 360,000 (ሦስት መቶ ስልሳ ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 2 ብር 10,000 (አስር ሺህ) ለሎት 3 ብር 12,600 (አስራ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ብር ) እና ለሎት 04 ብር 7,000 /ሰባት ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ. በቼክ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ወራቤ ከተማ ክልል ትምህርት ቢሮ ግዥና ንብረት አስ ዳይሬክቶሬት ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- የውል ማስከበሪያ - የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ7 ቀናት በኃላ ውሉን መፈረምና የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና አይነቶች ከፍያ በሚፈጸምበትየገንዘብ አይነት የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያነት ማስያዝ አለበት
- ቢሮው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታው ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጨረታው ውድድሩ በአሸናፊው የተሰጠው ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀናት ብቻ ነው።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046 771 0688 መጠየቅ ይችላሉ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከ/መንግስት ትም/ቢሮ
