Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት የእንስሳት መድኃኒት መገልገያ ዕቃ በዘርፉ ብቁ እና ህጋዊ ከሆኑ ንግድ ድርጅቶች በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡


 

ብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2018

 

በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት የእንስሳት መድኃኒት መገልገያ ዕቃ በዘርፉ ብቁ እና ህጋዊ ከሆኑ ንግድ ድርጅቶች በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት ተጫራቾች /ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል

  1. የንግድ ምዝገባ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  2. የአቅራቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  3. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  5. ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል
  6. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ
  7. ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ከሆነ አጫራቹ መ/ቤት በሚፈልጋቸው መጠን እና ጥራት የሚያቀርብና የመድኃኒቱ አገልግሎት ማብቂያ ጊዜው ግዥ ከተፈጸመበት ጊዜ አንስቶ ቢያንስ አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ መቆየት የሚችል መሆን ይኖርበታል፣
  8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ላይ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ዕቃ የአንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ በካፋ ዞን ሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ያስገባሉ።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  11. ጨረታው በ16ኛ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙ ይታሸጋል።
  12. ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካይ ያለመገኘት የጨረታውን መከፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
  13. አሸናፊው ድርጅት ያቀረበው ዕቃ ጥራቱና መጠኑ የተጓደለ ከሆነ አቅራቢው ድርጅት በራሱ ኪሳራ መቀየር የሚችል መሆን ይኖርበታል።
  14. የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን (CPO) ለተሸናፊው ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስከ 7ኛው ቀን ድረስ የውል ማስከበሪያ አስይዞ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ በሲፒኦ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
  15. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

 

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047 668 0200 /0431 በመደወል መረዳት ይቻላል።

 

በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender